የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር 52ኛ አመታዊ ጉባኤውን ሲያካሂድ ጉባኤውን በማሰመልከት አባላቶቹ የደምና የአይን ብሌን (Cornea) ልገሳ ከማድረጋቸው በተጨማሪ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 100 ሺህ ብር አበርክተዋል፡፡ የካቲት 3 2008 ጉባኤው በተከፈተበት እለት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን ጨምሮ ጉባኤው 8363፣ 8364 እና 8365 በመጫን ወገንተኝነታቸውን አሳይተዋል፡፡
ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ለ አትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዝዳንት ለዶ/ር አህመድ ረጃ የ 100 ሺህ ብር ቼክ አስረክበዋል፡፡ ወገናችንን በህክምናው በቅንነት እንደምናገለግል ሁሉ በችግሩም አብረን ነን በሚል ነው ይህ ልግስና የተደረገው፡፡ ዶ/ር ገመቺስ በዚህ ብቻም አናቆምም በተቻለን መጠን አባላትን በማስተባበር ወደ 200 ሺህ ብር ከፍ እናደርጋለን ብለዋል በቀይ መስቀል ማህበር ጽ/ት ቤት ለማህበሩ የተዘጋጀውን የምስጋና ሰርተፊኬት ሲቀበሉ፡፡